የኢትዮጵያ የTCDI የትምባሆ ቁጥጥር ድረ ገጽ

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣት መረጃን መሰረት ያደረገ ውሳኔን ለማጠናከር ከዴቨሎፕመንት ጌትዌይ (Development Gateway: an IREX Venture) ጋር በመተባበብር የኢትዮጵያን የትንባሆ ቁጥጥር ድረ ገጽን- (ethiopia.tobaccontroldata.org) እ.አ.አ ከ2021 ጀምሮ ሲያዘጋጅ ቆይቷል፡፡ ድረ ገጹ በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ የካቲት 21 ቀን 2015 ዓ.ም የሚመረቅ ሲሆን ሕግ አውጪዎችና ወሳኔ ሰጪ አካላት ትንባሆ ቁጥጥርን በሚመለከት የሚያስፈልጓቸውን መረጃዎች በአመቺ ሁኔታ ተደራሽ ለማድረግ የተዘጋጀ ነው፡፡ የኢትዮጵያው ድረ-ገጽ ዴቨሎፕመንት ጌትዌይ ከኬፕ ታውን ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ጥናት ክፍል (Research Unit on the Economics of Excisable Products (REEP)) ጋር በመተባበር ከሚያዘጋጃቸው አገር-ተኮር ከሆኑ ድረ ገጾች መካከል አንዱ ነው፡፡